አቡኒ ዮሐንስ
�አብሮነታችን ውበታችን � የቆዳ ውጤቶች መሸጥ እና ማካፋፈል
ጫማዎች መሸጥ ጀምረናል
20/11/2025
ጧት 3 ሰዓት አከባቢ ከአዳማ ሸገር ልመጣ ስል እጄ ላይ ካሽ ስለሌኝ በ ATM 2000 ብር አወጣሁና በለበስኩት Jeans ሱሪ ከኋላ ኪሴ እንደከተትኩ እየወጣ ያለ የቤት መኪና አገኘሁና ወጣን፤
መዳረሻዋ ቦሌ ስለሆነ ቦሌ ስንደርስ ደርሰናል ሂሳብ ስትለኝ ስንት ነው ስላት 550 እሽ ብዬ ከኋላ ኪሴ ከነበረው 2000 ላይ 600 ሰጠኋትና የቀረውን መልሼ ኪሴ አረኩት፤
መልስ 50 ዝርዝር ተቀብዬ ቦርሳዬ ውስጥ አርጌ የመገነኛ ታክሲ አግኝቼ መገነኛ ስሄድ የታክሲ 15 ብር አጠገቤ የነበረ ሰውዬ የኔንም ከፍሎልኝ እግዜር ይስጥልኝ እረ የሸገር ሰዎች ትለዩብኛላችሁ🥰 እያልኩ ከመገናኛ የአዲሱ ገበያ ባስ አግኝቼ ከዝርዝሩ ላይ 10 ብር ትከት ቆርጬ ተሳፈርኩ፤
ባስ ስሳፈር የመጀመሪያዬ ነው ሀዋሳ እኛ ሰፈር የምቆም ቆጪ ሁለት የምያክል ህዝብ ጥቅጥቅ ብሏል እዛ ውስጥ ያለው ፍቅር ደስ ይላል ግማሹ ይተቃቀፋል ፍቅራቸው እያስደነቀኝ አዲሱ ገበያ ደረስንና ወርጄ ሱሉልታ ታክሲጋ እየሄድኩ ከኋላዬን እደባብሳለሁ ወፍ😌
በሁለቱም ኪሶቼ እጄን ስከት ምንም የለም ቆም ብዬ አራቱንም ኪስ ስፈትሽ ኪሴ ባዶ ነው የምር ብዙም አልደበረኝም ሳቄና ንዴቴ አንድ ላይ መጣ😅
የሸገር ህዝብ እወዳችኋለሁ እባካችሁ 1400 ብሬን መልሱልኝ🥺
የ7 ቁጥር ምስጢራቶች
1. ሰባቱ አባቶች
ሀ. ሰማያዊ አባት እግዚአብሔር
ለ. የነብስ አባት
ሐ. ወላጅ አባት
መ. የክርስትና አባት
ሠ. የጡት አባት
ረ. የቆብ አባት
ሰ. የቀለም አባት
2. ሰባቱ ዲያቆናት
ሀ. ቅዱስ እስጢፋኖስ
ለ. ቅዱስ ፊልጶስ
ሐ. ቅዱስ ጵሮክሮስ
መ. ቅዱስ ጢምና
ሠ. ቅዱስ ኒቃሮና
ረ. ቅዱስ ጳርሜና
ሰ. ቅዱስ ኒቆላዎስ
3. ሰባቱ የጌታ ቃላት(እኔ ነኝ)
ሀ. የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ
ለ. የአለም ብርሃን እኔ ነኝ
ሐ. እኔ የበጎች በር ነኝ
መ. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
ሠ. ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ
ረ. እኔ መንገድ እና ህይወት ነኝ
ሰ. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ
4. ሰባቱ ሰማያት
ሀ. ጽርሐ አርያም
ለ. መንበረ መንግስት
ሐ. ሰማይ ውዱድ
መ. እየሩሳሌም ሰማያዊት
ሠ. ኢዮር
ረ. ራማ
ሰ. ኤረር
5.ሰባቱ ሊቃነ መላዕክት
ሀ. ቅዱስ ሚካኤል
ለ. ቅዱስ ገብርኤል
ሐ. ቅዱስ ሩፋኤል
መ. ቅዱስ ራጉኤል
ሠ. ቅዱስ ዑራኤል
ረ. ቅዱስ ፋኑኤል
ሰ. ቅዱስ ሰቂኤል
6. ሰባቱ አቢያተ ክርስቲያናት
ሀ. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
ለ. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
ሐ. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
መ. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
ሠ. የሴርዴስ ቤተ ክርስቲያን
ረ. የፊልድ ልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
ሰ. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን
7. ሰባቱ ተዓምራት
ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ ተዓምራት
ሀ. ፀሐይ ጨልሟል
ለ. ጨረቃ ደም ሆነ
ሐ. ከዋክብት ረገፉ
መ. አለቶች ተሰነጣጠቁ
ሠ. መቃብራት ተከፈቱ
ረ. ሙታን ተነሱ
ሰ. የቤተ መቅደስ መጋረጃ
8. ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት
ሀ. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
ለ. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
ሐ. ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ
መ. እነሆ ልጅሽ እናትህ እነሆት
ሠ. ተጠማሁ
ረ. ተፈፀመ
ሰ. አባት ሆይ ነብሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ
9. ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን
ሀ. ሚስጥረ ጥምቀት
ለ. ሚስጥረ ቁርባን
ሐ. ሚስጥረ ክህነት
መ. ሚስጥረ ሜሮን
ሠ. ሚስጥረ ተክሊል
ረ. ሚስጥረ ንሰሃ
ሰ. ሚስጥረ ቀንዲል
10. ሰባቱ አፅዋማት
ሀ. አብይ ፆም
ለ. የሐዋርያት ፆም
ሐ. የፍልሰታ ፆም
መ. ፆመ ነቢያት
ሠ. ፆመ ገሀድ
ረ. ፆመ ነነዌ
ሰ. ፆመ ድህነት
11. ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች
ሀ. ትዕቢተኛ አይን
ለ. ሐሰተኛ ምላስ
ሐ. ንፁህ ደምን የምታፈስ እጅ
መ. ክፉ ሐሳብ የምታፈልቅ ልብ
ሠ. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
ረ. የሐሰት ምስክርነት
ሰ. በወንድማማቾች መካከል ፀብን የምታፈራ ምላስ
12.ሰባቱ ፀሎተ ጊዜያት
ሀ. ነግህ (የጠዋት ፀሎት)
ለ. ሰለስት (የ 3 ሰዓት ፀሎት)
ሐ. ቀትር (የ 6 ሰዓት ፀሎት)
መ. ተሰዓቱ (የ 9 ሰዓት ፀሎት)
ሠ. ስርክ (የ 11 ሰዓት ፀሎት)
ረ. ነዋም (የመኝታ ፀሎት)
ሰ. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ፀሎት)
ወስብሀት ለእግዚአብሔር 🙏🙏🙏
08/05/2025
ወላጆች፣ ልብ ይበሉ!!!
| አንዲት መምህር የተማሪዎቿን የቤት ስራ እያረመች ነበር።
በዚህ መሀል፣ ባሏ በቤቱ እየተዘዋወረ፣ በስማርት ስልኩ ተተክሎ፣ የሚወደውን ጨዋታ በመጫወት ላይ ነበር።
የመጨረሻው የቤት ስራ ላይ ስትደርስ፣ መምህሯ በጸጥታ ማልቀስ ጀመረች።
ባሏ አስተውሎ ጠየቃት፦
— ምን ተፈጠረ?
እርሷም መለሰች፦
— ትናንት፣ ለተማሪዎቼ "ምኞቴ" የሚል የጽሑፍ ሥራ ሰጥቻቸው ነበር።
ባሏም አለ፦
— እሺ፣ ግን ለምንድነው የምታለቅሽው?
ሚስትየው እንባዋን ዋጥ አድርጋ መለሰች፦
— የመጨረሻውን ወረቀት ሳርም፣ ማልቀሴን መቆጣጠር አልቻልኩም።
ባሏ በጉጉት ጠየቀ፦
— እንዲህ ልብ የሚነካ ምን ተጽፎ ነበር?
ሚስትየው ማንበብ ጀመረች፦
ምኞቴ ስማርት ስልክ መሆን ነው።
ወላጆቼ ስማርት ስልካቸውን በጣም ይወዳሉ።
ለስማርት ስልካቸው የሚሰጡት እንክብካቤ በጣም ከመጠን ያለፈ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንድ ጊዜ እኔን መንከባከብ ይረሳሉ።
አባቴ ከሥራ ደክሞ ሲመጣ፣ ለስማርት ስልኩ ጊዜ አለው፣ ለእኔ ግን የለውም።
ወላጆቼ አንድ ጠቃሚ ነገር ሲሰሩ ስልኩ ሲደወል፣ ወዲያውኑ ያነሳሉ—
ለእኔ ግን እንደዛ አያደርጉም፣ እያለቀስኩም ቢሆን።
በስልካቸው ይጫወታሉ፣ ከእኔ ጋር ግን አይጫወቱም።
ከአንድ ሰው ጋር በስልክ ሲያወሩ፣ እኔን አይሰሙኝም፣ ጠቃሚ ነገር እየተናገርኩም ቢሆን።
ስለዚህ ምኞቴ ስማርት ስልክ መሆን ነው።
እነዚህን ቃላት ከሰማ በኋላ፣ ባሏ በጣም ተነካና ጠየቀ፦
— ይህንን ድርሰት ማን ነው የጻፈው?
ሚስትየው፣ አይኖቿ በእንባ ተሞልተው መለሰች፦
— ልጃችን።
ወላጆች፣ ይህንን አስታውሱ፦
የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ጠቃሚ ናቸው፣ ነገር ግን የተሠሩት ህይወታችንን ቀላል ለማድረግ ነው—
ለቤተሰባችንና ለምንወዳቸው ሰዎች ያለንን ፍቅር ለመተካት አይደለም።
ልጆች በዙሪያቸው የሚፈጠረውን ሁሉ ያያሉ ይሰማቸውማል።
ልምዶቻቸው አዕምሯቸውን ይቀርጻሉ እናም እድሜ ልክ የሚቆይ ምልክት ይተዋሉ።
ትክክለኛ በሆኑ የህይወት እሴቶችና በሐሰተኛ ፍላጎቶች ሳይጠመዱ እንዲያድጉ እንንከባከባቸው።
30/04/2025
ጎንደር አቡነ ሐራ ድንግል ቤተከርስቲያን ማራኪ ግቢ ቀራኒዮ መድሐኒአለም ቤተከርስቲያን ካሜራ ማኑን ግን😍
30/04/2025
በጣም አስገራሚ ና አስተማሪ ታሪክ ነው አምብቡት
_
አንዱ ሚስቱን ይመታታል። በአጋጣሚ ሊገድላት ሳያስብ በእጁ
ትሞትበታለች። ጉዳዩ ይፋ ወጥቶ ዕዳ እንዳይኾንበት ምን
ማድረግ እንዳለበት ያስባል። አስቦ አሰላስሎ በስተመጨረሻም
አንድ ሀሳብ መጣለት። እርሱም ወደሰፈራቸው አዋቂ ነኝ ባይ
ሰው
ጋርመሄድ ነበር። ታዲያ ይሄ አዋቂ ተብዬ ሰውም መፍትሄ
የሚለውን ሀሳብ እንዲህ ሲል ይመክረዋል፦
ደጅህ ላይ ተቀምጥና ቆንጆ ወጣት ሲያልፍ ካየህ "አንዳች
የምታግዘኝ ነገር አለ" በለውና ወደ ቤትህ አስገባው።ከዚያም
ግደለውና ከባለቤትህ እሬሳ ጋር አጠገብ ለአጠገብ
አጋድመው።
የርሷን ቤተሰቦች ጥራና "ከዚህ ወጣት ጋር ሲያመነዝሩ
ስመለከት
እራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ እርምጃ ስወስድባቸው በእጄ ሞቱ"
ብለህ ንገራቸው አለው።
አባ ውራውም መላ ነው ተብሎ የተነገረውን ተቀብሎ ደጃፉ ላይ
ሄዶ ቁጭ ብሎ መጠባበቅ ይጀምራል። ብዙም ሳይቆይ አንድ
ወጣት በአጠገቡ ሲያልፍ ተመለከተና "ወንድም አንዴ
ላስቸግርህ? የሆነች ነገር እንድታግዘኝ ፈልጌህ ነበር" ብሎ
አስማምቶ ወደ ቤት ያስገባዋል። እንደተመከረውም ይገድለውና
ከሚስቱ ጀነዛ አጠገብ ያጋድመዋል።
የሚስቱ ቤተዘመዶች ሲመጡም በዝሙት ላይ አግኝቷቸው
ራሱን
መቆጣጠር አቅቶት እርምጃ እንደወሰደባቸው ይነግራቸዋል።
እነርሱም ጥፋተኛ ሳያደርጉት ምክኒያቱን ይረዱትና ይተዉታል።
ይሄንን የማምለጫ ዘዴ ነግሮት የነበረው ሰውዬ ገዳዩ ከምን
እንደደረሰ ሊጠይቀው ቤቱ ይከሰታል። ገዳዩ ሰውዬም
የመከረውን
እንዳደረገና እንደተሳካለት በኩራትና በምስጋና ይነግረዋል።
እስኪ
የገደልከውን ልጅ አሳየኝ ብሎ አዋቂ ተብዬው ይጠይቀዋል።
ገዳዩ ወስዶ ሲያሳየውም
ለካስ የተገደለው የራሱ የአዋቂ ነኝ ባዩ ልጅ ኖሯል! በሳሉት
ቢለዋ
መቆረጥ ይሉሃል እንደዚህ ነው!
ለተንኮል ሰይፉን የሳለ እራሱ ይቆረጥበታል። ለወንድሙ ጉድጓድ
የቆፈረ ራሱ ይገባበታል። የሌሎችን ነውር አደባባይ የሚበትን
የራሱ ነውር አደባባይ ይታይበታል።
ከተመቻችሁ ሼር አድርጉት!
28/04/2025
ተሳፋሪዎቹ እና አውሮፕላኑ !!!
ተሳፋሪዎቹ ወደ ጣልያን እየበረሩ ሳለ የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያ አንድ ነገር ተናገረ " ክብራንና ክብራት ይህን ስናገር ባጣም አዝናለው አንደኛው የአውሮፕላኑ ሞተር አይሰራም ሀለተኛውም ቆሞአል በጥቂት ደቂቃዎች የመከስከስ አደጋ ይደርስብናል ግዜው የመናዘዝና የይቅርታ ግዜ ነው እናም ባለችን ትንሽ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፣ እርስ በርስ ይቅር ተባባሉ ንስሃ ግቡ ማስተካከል ያለባችሁን ነገር አስተካክሉ " አላቸው።
ከተሳፋሪዎቹ ውስጥም ሁለት ባልና ሚስት ነበሩ ባል የሚስቱን እጅ ጭብጥ አድርጎ ይዞ.. የኔ ማር ይቅር በይኝ ይቅር በይኝ በጣም በጣም በድዬሻለሁ ታውቂያለሽ ከእኛ ጋር የምትኖረው እህትሽ አብሬያት እተኛ ነበር። አልደብቅሽም ከእሷ ጋር በስሜት ተጣጥመን በፍቅር ወድቀን ነበር። ብዙ ግዜ አስወርዳለች ከጣልያን ስንመለስ አንቺን በመርዝ ገድላ ወደ አሜሪካ ሄደን አብረን እንድንኖር አቅዳ እኔም በእቅዷ ተስማቼ ነበር። እባክሽ አንቺ የሦስት ልጆቼ እናት ነሽና ይቅር በይኝ ....
ሚስትም በተራዋ የባሏን እጅ ጥብቅ አርጋ ይዛ ...የኔ ውድ ምንም ማለት አይደለም ይቅር ብየሃለው ግን እኔም የምናዘዘው ነገር አለኝ .. እባክህ ይቅር በለኝ.. አ አሁን ካሉን ሦስት ልጆች መሃከል ሁለቱ ያንተ ልጆች አይደሉም ያንተ ልጅ ሴቷ ብቻ ናት የቀሩት ስንጋባ አንደኛ ሚዜህ የነበረው ውድ ጓደኛህ ናቸው።
የኔ ውድ ታስታውሳለህ አንዴ ሌቦች አልዘረፉህም ?
ባል .... አዎ የኔ ማር አስታውሳለው
ሚስት .... እነዛን ሌቦች የላኩትና እንዲዘርፉ ያደረኩት እኔ ነኝ ምክንያቱም እሱ የትምህርት ክፍያ አልነበረውም ያ ካንተ የተዘረፍከው ገንዘብ ለእሱ የትምህርት ክፍያ ውሏል።
እኛም ደግማ ከጣልያን እንደተመለስን አንተን ለማስገደል ሰው ቀጥረን ነበርና ....... እባክህ ውዴ የሥጋ ምኞት አሳስቶኝ ነውና ይቅር በለኝ...... ባል.... ምንም አይደል የዋልሽብኝ በደል ከግፍም የከፋ ግፍ ቢሆንም. ይቅር መባባል ነውና ያለብን ይቅር ብዬሻለው።
በዚህ ሰዓት ድንገት የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያው ድምፁ ተሰማ "ክቡራንና ክቡራት እናንተ በእውነት እግዚአብሔር ይወዳችኋል ስለሚወዳችሁም ጸሎታችሁን ሰምቷል ሁለቱም ሞተሮች አሁን እንደ በፊቱ በትክክል መስራት ጀምረዋል በሰላም እናርፋለን እንኳን ደስ አላችሁ።
ሁሉም ተሳፋሪዎች መጀመሪያ ከነገራቸው መጥፎ ዜና ይልቅ አሁን የነገራቸው መልካም ነገር እረበሻቸው ከመደሰት ይልቅ የተናዘዙት ኃጢአታቸው አሳፍሯቸው ፀጥ አሉ።
አንድ ተሳፋሪ በድንገት ብድግ አለና አብራሪ ስማ.... አብራሪ ስማ .... ማረፍ የለብንም ...... ማረፍ የለብንም..... አውሮፕላኑን ከስክሰው ...... ከስክሰው ....ጣለው ....ጣለው .......ሲል ሁሉም ተሳፋሪዎች በአንድ ድምፅ ፈጥፍጠው ........ ከስክሰው........ ጣለው ...... እያሉ ይጮኹ ጀመር !!
ምን ተሰማችሁ ?????? ኃጥያት አስቀያሚ
ነው አይደል!! ቢሆንም በንስኃ ግቡ
20/04/2025
እጅግ በጣም ደስ የሚል ዜና 🎊🎊🎊
በጣም ደስ ብሎኛል አብራችሁ ጃጁ ትልቅ ውሳኔ ነው👏
😳😳
ውይ ኩላሊት🙄😂😂
የቅናት መጨረሻ🙄🙆♀️
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
ቂርቆስ
Addis Ababa
021